ዲሞክራሲ እስከ ጥግ ድረስ
ይስሐቅ ገ/ግዛቤር
የአሜሪካ የኮንግረሱ አፈጉባኤ የሆኑት ጆን አንድሪው ከፕሬዝዳንት በራክ ኦባማ ውጭ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚንስትር ቢንያሚን ኔትናሆን ኮንግረሱ ፊት ስለ ኢራን ኒኩለር ፕሮግራም ንግግር እንዲያደርጉ ጋበዟቸው᎓᎓ታድያ ይሀንን ነገር ኦባማ ባወቁ ግዜ በጣም ነው የተናገሩት ምክንያታቸው ደሞ ቢንያም ኔትናሆ ከሁለት ወር በኋላ ባገራቸው ላይ ምርጫ ያካሄዳላ እና ይህ ኮንግረሱ ፊት የሚያደርጉት ንግግር ለምርጫ መጠቀምያ ነው ይላሉ᎓᎓ፕሪዝዳንቱ ግን ግብዣውን ከመቃወም ውጭ ምንም ማድረግ አይችሉም ለምን ቢባል ህገ መንግስቱ አይፈቅድላቸውምና ይሄንን ግብዣ ወደኛ ሀገር ብንወስደው ብዬ አሰብኩት᎓᎓
99.9% የኢሃዲግ አባል የተሰበሰቡበት ፓርላማ ላይ የቀድሞ ጄኔራል ያሁኑ አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ያለ ጠቅላ ሚንስትሩ አማካሪዎች እነ አቦይ ጸሐዬን ወይ እነ አርከበ እቁባይን ሳያማክሩ ወይም ያለነሱ ፈቃድ የሱማሊን ፕሪዝዳንት ሀሰን ሼክን በፓርላማ ላይ ስለ አልሸባብ ንግግር እንዲያደርጉ ቢጋብዟቸው አቶ አባዱላን ህውሀቶች ምን አይነት ክስ ሊያዘጋጁላቸው ይችላሉ
ሀ/አገር በመክዳት
ለ/ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት በማድረግ
ሐ/በሙስና ወይንስ
መ/በስነ ምግባር ጉድለት
መልሱን ላንባቢዎች ትቸዋለሁኝ የወያኔ መንግስት በኢኮኖሚ እድገት እንጂ ከሀገሮች ጋር ፉክክሩ ከዲሞክራሲ እድገት ጋር እሱን አይመለከተውም ሳይንሱ ደሞ ያለ ዲሞክራሲ እድገት ኢኮኖሚ ሊያድግ አይችልም᎓᎓ወያኔ የያዘው ደሞ እሱ የመረጠውን ቡድንና ግለሰብ ሀብታም ማድረግ ነው ያደሞ ለሀገር ውድቀት እንጂ እድገትን አያመጣም᎓᎓
No comments:
Post a Comment