Tuesday, February 24, 2015

100 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በናይሮቢ ኬንያ ለእስር ተዳረጉ

በትላንትናው ምሽት ቁጥራችው 100 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች  በናይሮቢ ኬንያ ለእስር ተዳረጉ᎓᎓ስደተኞቹ በወያኔ መንግስት ምክንያት  ባገራቸው ላይ የመኖር ዋስትና ስላጡ የመጨረሻውን አማራጭ መሰደድን መረጡ ጉዞው ረጅም ነበር ወደ ደቡብ አፍሪካ ግን ምን ዋጋ አለው ገና ከናይሮቢ እስር ገጠማቸው ተከራይተው በሚኖሩበት ቤት ተጠቁሞባቸው ፖሊስ ወደ እስር ቤት ወሰዳቸው የሚገርመው እስርን፣እንግልትን፣መከራንና የበታችነትን ሽሽት ነበር የተሰደዱት ያም ግን በሄዱበት ተከተላቸው መቼ ይሆን ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን የስደት እስር የምንወጣው የአፍሪካን እስር ቤት የሞላው ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሆነ የወያኔ መንግስት እንደው አይደለም በጎረቤት ሃገር እስር ላይ ላሉ ሊሞገት አገር ውስጥም ያለውን ህዝብ አስሮ ሊጨርስ ነው᎓᎓አቤቱ ዲሞክራሲይቱ ኢትዮጵያ መቼ ይሆን የምትወለደው??

No comments:

Post a Comment