Saturday, February 21, 2015
የካቲት 12 እናስበው
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም - ለኢጣሊያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንድ ልዑል በመወለዱ ምክንያት በጄነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ከተሰበሰቡት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ለፋሺስቶቹ ያደሩ ከሀዲ ባንዳዎችና መኳንንት፤ የፋሺስት ባለ ሥልጣናት ወታደሮች በተሰበሰቡበት መኻል፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የእጅ ቦምብ ወርውረው አደጋ ሲጥሉ ግራዚያኒን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል። ይኸንን ድርጊት በመበቀል ሰበብ እዚያው ግቢ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጨፈጨፉ፤ ቀጥሎም የተማሩ ወጣቶች፣ የጦር መኮንኖችና ካህናት፣ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት በሙሉ እየተለቀሙ ተጨፈጨፉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቤት ውስጥ እያስገቡ ከውጭ ቆልፈው ቤንዚን እያርከፈከፉ አቃጠሉአቸው። በአካፋ፣ በዶማ፣ በመጥረቢያ በተገኙበት ኢትዮጵያውያንን እየቆራረጡ የደም ጎርፍ አወረዱ። ፋሽስቶች የአዲስ አበባንና የአካባቢውን ሕዝብ በጅምላ ጨፈጨፉት። በሶስት ቀናት 30ሺህ ሕዝብ መስዋዕትነት ተቀበለ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment