በሊብያ አገር IS የሚባለው አሸባሪ 30 ኢትዮጵያና ኤርትራ ወንድሞቻችንን ባሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል ሀዘኑ ለቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው᎓᎓በባህላችን ደሞ ለቅሶ መድረስ እና ማስተዛዘን ያለና የሚኖር ነው ግን አሁን የማየው ነገር ወደ ማስታወቂያቃ(Business)እየቀየሩት ነው᎓᎓
ዮሴፍ ገብሬ(Josy in the house)የሚባለው ግለሰብ በሀዘነተኛ ቤተቦች ላይ ፕሮግራሙን ሲሰራ ተመልክቺ በጣም ነው ያናደደኝ᎓᎓እንዴት ነው ካሜራ ይዞ ተዘጋጅቶ ለቅሶ ለመድረስ የሚሄደው ከመሄዱም በተጨማሪ ለሃዘነተኞቹ ይሄን ያህል ብር በካሽ ይሂን ያህል ደሞ ያኑረው᎓᎓ከባንክ የሚወጣ ከjosy in the house የተበረከተ ሲሆን ከጀማሪ ኢንቨስተር ከአቶ እገሌና ከወዳጆቼ በማስተባበር አበርክቻለሁኝ ብሎ ለሃዘነተኛው ብር ሲሰጥ ይታያል᎓᎓
ጆሲ ቢገባው እኮ በባህላችን ቤተሰቦቻችን እዝን ሲወስዱ እንጀራውን በጨርቅ ተሸፍኖ ወጡም እንዲሁ በዳንቴል ተሸፍኖ ሀዘነተኛው እንኳን ለእዝን ምን እንደመጣ አያቅም ሲበላም ተቀላቅሎ ነው የማን ምን እንደሆነ አይታወቅም ሌላው ለሀዘነተኛው ብር ሲሰጥ ቀስ ብሎ ሰው ሳያይ ነው የሚሰጠው እንጂ እዩልኝ እየተባለ አይደለም ባደባባይ መርዳት ካስፈለገም መጀመርያ ሀዘነተኛውን በስነስርአት ጠይቆና አስፈቅዶ እንጂ በደካማ ጎን ገብቶ የራሱን business ማጧጧፍ አይደለም እኔ ለምን እረዳ አይደለም የምለው ግን ሀዘን ቤቱን ለምን josy show ፕሮግራም ያደርገዋል እኔ የምፈራው የቀሩት የ show አዘጋጆችም ሀዘናችንን የነሱን business እንዳያጧጡፉት እፈራለሁኝ᎓᎓
ለሞች ቤተሰቦች መጽናናትንና ለተሰዉትም ወንድሞቻችን ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ፈጣሪ ያኑረው᎓᎓
No comments:
Post a Comment