Tuesday, April 28, 2015

ዘመነኛ ዲሞክራሲ

                                          



  
  ዘመነኛ ዲሞክራሲ                           ይስሐቅ  ገ/ግዛብሔር

በአለማችን ካሉ ሀገራት ውስጥ አብዛኛዎቹ ሀገራት ምርጫ ያካሄዳሉ ካብዛኛው ሀገራት ውስጥ ጥቂቱ ነው ዲሞክራሲያዊ  የተሞላበት ምርጫ የሚካሄዱት ለጹህፌ መነሻ የሆነኝ አፍሪቃ ውስጥ ለሚካሄደው የይስሙላህ ምርጫ ነው
 እንደምናውቀው አፍሪቃ ውስጥ ከጥቂት ሀገራት ውጭ አብዛኛው የአባ ገነን መንግስት የሰፈረባት አህጉር ነች እነዚህ አባገነኖች አሁን የያዙት በማስመሰል ምርጫ እያሉ ስልጣናቸውን ማራዘምና ህዝቡን መጨቆን ነው ሊላው በጣም የሚገርመው እነዚህ አንባገነን መንግስታት ምርጫ የሚያደርጉት አንድ ወቅት መሆኑ  ለምሳሌ ብንመለከት 
1/የሱዳኑ መንግስት ኦማር አልበሽር(Omar al-Bashir)ፓርቲያቸው National congeries party       ስልጣን ላይ ከወጣ ከ15 ዓመት በላይ ሆነው በዚህ ወር ባደረጉትም ምርጫ እንኳን ዋና ዋና ተቃዋሚዎች በሌሉበት 94% አሸንፈው አረፉት

2\የቶጎ መንግስት ፋውሪ ስለጣን ከያዘ 3 የምርጫ ጊዜ አሸንፎል የፊታችን ቅዳሜ በሚካሄደው ምርጫ ካሸነፉ አባታቸው ለ 38 ዓመት የመሯትን አገር እሳቸው ከነ ቤተሰባቸው ለ 50ዓመት ህዝቡን ሊገዙ ነው

3/የብሩንዲ መንግስት ፔሪ ንኩርንዚዛ ያገሩ ህገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ ለ 3ኛ ግዜ  በ June 26 ለሚካሄደው ምርጫ እንደሚወዳደሩ ፓርቲያቸው መግለጫ ሰቶ ባገሩ ለይ እረብሻ ተነሳ ለብዙ አመት
በርስ በርስ ጦርነት የምትታወቅ ሃገር ነች

4/የኢትዮጲያ መንግስት ወያኔ ኢትዮጵያን መግዛት ከጀመረ 24ዓመት ሆነው  3 ግዜ በተጭበረበረ ምርጫ በማሸነፍ አሁንም የፊታችን ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ከወዲሁ ያሰጉኛል የሚላቸውን ግለሰብና ቡድኖች በማሰር ላይ ይገኛል

Thursday, April 23, 2015

በሀዘናችን አትነግዱ



ይስሐቅ ገ/እዛብሔር


በሊብያ አገር IS የሚባለው አሸባሪ 30 ኢትዮጵያና ኤርትራ ወንድሞቻችንን ባሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል ሀዘኑ ለቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው᎓᎓በባህላችን ደሞ ለቅሶ መድረስ እና ማስተዛዘን ያለና የሚኖር ነው ግን አሁን የማየው ነገር ወደ ማስታወቂያቃ(Business)እየቀየሩት ነው᎓᎓
  ዮሴፍ ገብሬ(Josy in the house)የሚባለው ግለሰብ በሀዘነተኛ ቤተቦች ላይ ፕሮግራሙን ሲሰራ ተመልክቺ በጣም ነው ያናደደኝ᎓᎓እንዴት ነው ካሜራ ይዞ ተዘጋጅቶ ለቅሶ ለመድረስ የሚሄደው ከመሄዱም በተጨማሪ ለሃዘነተኞቹ ይሄን ያህል ብር በካሽ ይሂን ያህል ደሞ ያኑረው᎓᎓ከባንክ የሚወጣ ከjosy in the house የተበረከተ ሲሆን ከጀማሪ ኢንቨስተር ከአቶ እገሌና ከወዳጆቼ በማስተባበር አበርክቻለሁኝ ብሎ ለሃዘነተኛው ብር ሲሰጥ ይታያል᎓᎓
  ጆሲ ቢገባው እኮ በባህላችን ቤተሰቦቻችን እዝን ሲወስዱ እንጀራውን በጨርቅ ተሸፍኖ ወጡም እንዲሁ በዳንቴል ተሸፍኖ ሀዘነተኛው እንኳን ለእዝን ምን እንደመጣ አያቅም ሲበላም ተቀላቅሎ ነው የማን ምን እንደሆነ አይታወቅም ሌላው ለሀዘነተኛው ብር ሲሰጥ ቀስ ብሎ ሰው ሳያይ ነው የሚሰጠው እንጂ እዩልኝ እየተባለ አይደለም ባደባባይ መርዳት ካስፈለገም መጀመርያ ሀዘነተኛውን በስነስርአት ጠይቆና አስፈቅዶ እንጂ በደካማ ጎን ገብቶ የራሱን business ማጧጧፍ አይደለም እኔ ለምን እረዳ አይደለም የምለው ግን ሀዘን ቤቱን  ለምን josy show  ፕሮግራም ያደርገዋል እኔ የምፈራው የቀሩት የ show አዘጋጆችም ሀዘናችንን የነሱን business እንዳያጧጡፉት  እፈራለሁኝ᎓᎓
ለሞች ቤተሰቦች መጽናናትንና ለተሰዉትም ወንድሞቻችን ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ፈጣሪ ያኑረው᎓᎓

Wednesday, April 22, 2015

እረ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ

የወያኔ መንግስ በዛሬው እለት እራሱ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሲዋረድ ተመለከተ እውነት በሐሰት አትቀየርም እንደሚባለው ህዝቡ ባገኘው አጋጣሚ ብሶቱን ሲያሰማ የፌዴራል ወታደር ግን ከisis ባልተናነሰ በያዘው ቆመጥ ወጣት ሳይል አሮጊ በመደብደብ ህዝቡ ላይ ጉዳት አደረሱ ይሄ ሁሉ ለምን?እውነት ስለተናገሩ የወያኔን ጭካኔ በዘፈን ስላሰሙ
 ይለያል ይለያል ይለያል ዘንድሮ
የወያኔ ኑሮ
የባንዳዎ ኑሮ
የካሀዲ ኑሮ᎐᎐᎐
ቢገባቸው ኑሮ ፌዴራል ፖሊሱም ከወገኑ ጋር ነበር መቆ
ም የነበረበት
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዛብሄር ትዘረጋለች




Monday, April 20, 2015

አሸባሪው ቡድን ‘አይኤስአይኤስ’ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያንን ገደለ የሟች ቤተሰቦች ሐዘን ተቀምጠዋል - በኢንተርኔት ፎቶና ቪዲዮ አይተው



በሊቢያ የአሸባሪው ቡድን ‘አይኤስአይኤስ’ ታጣቂዎች፣ ’30 ኢትዮጵያዊያን ክርስትያኖችን ገድለናል’ ብለው በቪዲዮ የተቀረፀ አሰቃቂ የጭካኔ ግድያ ያሰራጩት በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ነው። በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በደረሰው ዘረኛ ጥቃት ማግስት፣ በሊቢያ ሲቪል ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የተፈፀመው የአሸባሪ ቡድን ዘግናኝ ግድያ፤ የኢትዮጵያውያን ሐዘንና ቁጭት አክብዶታል። 
በኢንተርኔት የተሰራጨው ቪዲዮና ፎቶ፣ የሟቾቹን ማንነት ወዲያውኑ ለማወቅና ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለብዙዎች አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ለቤተሰቦች ግን አጠራጣሪ አልነበረም። ወላጆችና ቤተሰብ፣ ወንድምና እህት፣ ጎረቤትና ወዳጆች ሁሉ ውስጥን በሚያደማ ቅፅበታዊ ሐዘን ነው የተመቱት።  
በአዲስ አበባ የኢያሱ ይኩኖአምላክ እና የባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ድንገተኛ መርዶ የደረሳቸው እሁድ እለት ነው። በሰላሳዎቹ ዕድሜ ላይ የነበሩት ኢያሱና ባልቻ በአንድ ሰፈር ውስጥ ያደጉ ጎረቤታሞች ናቸው - በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 25፤ በአሁኑ ወረዳ 10። የሟቾቹ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ለቅሶውም አንድ ላይ ነው፡፡
ኢያሱና ባልቻ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ወደ ሊቢያ የሄዱት አንድ ላይ እንደሆነ የገለፀልን የኢያሱ ወንድም፤ የሊቢያውን የግድያ ወሬ የሰማው እሁድ ዕለት ነው - ስልክ ተደውሎ። የደወለለት ሰው፣ “የናንተ ሰፈር ልጆች ሊታረዱ ሲሉ የሚያሳይ ፎቶ በፌስቡክ ተለጥፏል” ብሎ ሲነግረው፤ በደንጋጤ “እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀ። “የወንድሜን ስም ጨምሮ ነገረኝ፤ የወንድሜን ስም አያውቅም ነበር” ይላል የኢያሱ ወንድም። 
“የኔ ፌስቡክ ስለማይሰራ ጓደኛዬ ጋር ሄጄ አየሁ። በደንብ ስላልታየኝ እንደገና ከምሽቱ አራት ሰአት ስንከፍት ወንድሜን ተንበርክኮ አየሁት። ባልቻን ደግሞ ቀይ ቱታ ካደረጉት መሀል ለየሁት፡፡ ለእናቴ ከመንገሬ በፊት ለሩቅ ዘመዶች ለመናገር እያሰብኩ እያለ እነሱ ቀድመው ሰምተው ለቅሶ ላይ አገኘኋቸው” ብሏል የኢያሱ ወንድም። 
ኢያሱ ኳታር ሰርቶ የተወሰነ ገንዘብ ይዞ ስለመጣ የባልቻንም ወጪ ሸፍኖለት ነው አብረው የሄዱት። ከኢትዮጵያ ወጥተው በሱዳን ጉዞ የጀመሩት ከሁለት ወር በፊት ነው። “ሱዳን እያሉ በስልክ እንገናኝ ነበር። ገንዘብ ሲያስፈልጋቸው እልክላቸው ነበር” የሚለው የኢያሱ ወንድም፤ “ወደ ሊቢያ ከተሻገሩ በኋላ ግን ስልክ ቁጥር እሰጥሃለሁ ቢለኝም አንገናኝም ነበር” ብሏል።  
  

Thursday, April 16, 2015

ኢሉሄ ኢሉሄ


ይሄ ነበር አፓርታዳይዝ ነጮች በጥቁሮች ላይ በገዛ አገራቸው ላይ ሲጨቆኑ
የነሱን ጭቆና እኛ ኢትዮጵያን ተረድተን እነሱን ነጻ ለማውጣት አብረን ታገልን
ነጻነታቸው ነጻነታችን ደስታቸው ደስታችን ነበር
በመጨረሻ ሰዓት እጃቸው እኛ ላይ በረታ