Sunday, March 29, 2015

በየመን ኢትዮጵያውያኖች በጭንቅ ላይ ናቸው * ግማሾች እንቅልፍ አጥተው ነው የሚያድሩት…




ግሩም ተ/ሀይማኖት (ከየመን)
ረቡዕ ሌሊት 8፡30 ላይ የተጀመረው የአየር ድብደባ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የመን ነዋሪ የሆነ ሁሉ በፍርሃት ርዷል፡፡ በተለይ በትላንትናው ሌሊት የነበረው የአየር ድብደባ ከፍተኛ ስለሆነ ህዝቡ ላይ የጣለው ፍርሃት ከወትሮው የተለየ ነው፡፡ “በሁቲይን አማጽያን ሚሊሻ ላይ የተጀመረው የአየርጥቃት አሁንም በድርድሩ ካልተስማሙ ወይ ሰነዓ ከተማን ለቀው እስካወጡ አያቆምም!” ሲሉ የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ ገልጸዋል፡፡ ይህን አባባላቸውን ተከትሎ እግረኛ ሰራዊትም ሊንቀሳቀስ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡ 20.000 እግረኛ ወታደር ተዘጋጅቶ ድንበር ላይ መሆኑን የየመን መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ተጀምሮ የነበረውን ድርድር እንዲቀበሉ ለሁቲይን አማጺዎች ከትላንት ወዲያ የ3 ቀን እድሜ ቢሰጣቸውም አልተቀበሉትም፡፡
በሳዑዲ ሰብሳቢነት የአረብ ሊግ ሀገራት መንግስታት በየመን ጉዳይ ለመመከር ግብጽ ሻርማ ሸኸ ተሰብስበው ነው ያሉት። በዚህ ስብሰባ ላይ የአየር ጥቃቱ የዘመቻ መሪ ሀገር የሳዑዲ አረቢ ንጉስ ሰልማን ሀቲይን የተባሉት አማጽያን ለቀው እስኪወጡና የመን እስክትረጋጋ ድረስ የተጀመረው ጥቃት ቀጣይ እንደሆነ ገልጸዋል በማለት የየመኑ ቶውራ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የየመኑ መሪ አብድረቡ መንሱር ሀዴ ተገኝተዋል፡፡ ህዝቡ ግን ሀገራችንን እያስደበደበ ያለው ፕሬዘዳንታችን ነው በማለት ጥስ እየነከሰባቸው ነው፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት አሊ አብደላ ሳላ ድርድሩን እንደሚቀበሉ ቢገልጹም ተቀባይነት ያገኙ አይመስልም፡፡
ዛሬ ሌሊት በሳውዲ የተመራው የአስሩ ሀገራት ህብረት ጦር በሰንዓ ፈጂ አጣን የተባለው ቦታ ጋራ ላይ የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ያለ የብላስቲክ ሚሳየል ክምችት ማውደሙ ታውቋል፡፡ ይህ የመሳሪያ ክምችት በተመታበት ወቅት መላ ከተማው የተርገደገደበት የመሬት መንቀጥቀጥ አይነት ሁኔታ ነበር፡፡ አንዳንድ ህንጻዎች መስታዎታቸው ሁሉ ርግፏል፡፡ ነዋሪው ሲነጋ እንቅልፍ አጥቶ መደሩ ዋነኛው ርዕስ ነበር፡፡ በተለይ ስደተኛ ኢትዮጵያዊን ከፍተኛ ፍርሃት ተውጠን እንዳለን በርካታ ያናገርኳቸው ወገኖቼ ገልጸውልኛል፡፡ በእርግጥ ሌላውስ ወገን የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያንን እንዴት እያሰባቸው ይሆን?
የተመታው ካምፕ ላይ የሚቃጠለው መሳሪያ ፍንዳታም ከፍተኛ ነበር፡፡ ከሌሊቱ 8፡20 ጀምሮ ጠዋት ድረስ እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ነበር፡፡ የሁቲይን አማጺያን ድብደባውን በዝምታ እያዩት አይደለም፡፡ ከየአቅጣጫው በአየር መቃወሚያ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ እንደ አባባላቸው ከሆነ የአየር ጥቃቱን ከሚያደርሱት ጀቶች እስካሁን ሁለት መምታታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ሌሊት ሰነዓ ላይ ድብደባው ቀነስ ቢልም ሁዴዳና ሌሎች ደቡባዊ የመን ላይ ጠንከር ያለ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሁቲይኖቹም ከየአቅጣጫው የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ሙከራቸው በዛሬው ሌሊት ቀንሶ ታይቷል፡፡ ሰነዓ ያለ ኢትዮጵያዊ በጭንቅ ውስጥ ሲሆን አደን የተባለው ሁለተኛ ከተማ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊን በከፍተኛ ሁኔታ እያነቡ ነው፡፡

Tuesday, March 24, 2015

ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ

‹‹ቤተሰቦቻቸው ምግብና ልብስ ማስገባታቸውን ሰምተናል››  ሰማያዊ ፓርቲ
የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ የምክር ቤት አባል የነበረችው ወ/ሪት ኢየሩሳሌም ተስፋውና የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል አቶ ፍቅረ ማርያም አስማማው ትክክለኛ ቀኑ ባይታወቅም፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት ድንበር አቋርጠው ኤርትራ በመግባት ግንቦት ሰባትን ሊቀላቀሉ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ፡፡
የፓርቲው አባላት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የ28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው መሆኑ እየተነገረ ቢሆንም መቼ፣ እንዴትና በማን ተይዘው የትኛው ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ሪፖርተር ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
በቁጥጥር ሥር ውለዋል ስለተባሉት ሦስቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ የፓርቲያቸውን አባላት መታሰር የሰሙ ቢሆንም በቂ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ የተጨበጠ ነገር ማግኘት እንደተሳናቸው የሚናገሩት አቶ ዮናታን፣ ቤተሰቦቻቸው ምግብና ልብስ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) እንደወሰዱላቸው መስማታቸውን ጠቁመው፣ በአካል ያግኟቸው አያግኟቸው ግን እንዳላወቁ አስረድተዋል፡፡
እሳቸው ግን መቼ እንደታሰሩና የት እንደታሰሩ አለማወቃቸውንና ከ15 ቀናት በፊት ሌላ የፓርቲው ተወዳዳሪ ዕጩ መታሰሩን አስታውሰው፣ ምናልባት በዚያን ጊዜ ታስረው ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሁዳዴን ፆም በጸሎት ለማሳለፍ እንደሄዱ የሚናገሩት አቶ ዮናታን፣ የትና መቼ እንደሄዱ ግን ግልጽ አላደረጉም፡፡ በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተባሉት አባላት ቀደም ባሉት ጊዜያት ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉና በፓርቲው ውስጥ ኃላፊነት የነበራቸው ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ከኃላፊነት ተነስተው አባል ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ 
አቶ ፍቅረ ማርያም ግን እስካለፈው ሳምንት ድረስ ሥራ ላይ እንደነበሩ አቶ ዮናታን ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ብዙ ሰዎች በየድረ ገጹ ብዙ ነገር ይጽፋሉ፡፡ ትክክለኛውን ነገር ግን ማግኘት አቅቶናል፤›› የሚሉት አቶ ዮናታን፣ ማዕከላዊ ምርመራ ሄደውም ሆነ ሰው ልከው ምንም ያገኙት ምላሽ ባለመኖሩ፣ እስከሚጣራ ድረስ አስተያየት መስጠት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ 
ጊዜው የምርጫ ወቅት በመሆኑ በጣም ሥራ እንደሚበዛባቸው ገልጸው፣ አሁን መናገር ባይችሉም ወደፊት ሁኔታውን ተከታትለው ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ 
ምንም እንኳ ሦስቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በጎንደር በኩል አድርገው ወደ ኤርትራ ለመሻገር ሲንቀሳቀሱ ድንበር አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸውን ፓርቲው ቢያውቀውም፣ የተፈጠረውን ጉዳይ ለምን ይፋ አያደርግም ተብሎ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ወቀሳ እየቀረበበት ነው፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉትን የአባላቱን ጉዳይ በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ አለመስጠታቸው ያበሳጫቸው የተለያዩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካለፈው ዓርብ ሌሊት ድረስ ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኙም፡፡
ኤርትራ በመግባት ግንቦት ሰባት የተባለውን ድርጅት ለመቀላቀል ድንበር አካባቢ ተይዘዋል ስለተባሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በመንግሥት በኩልም እስከ ዓርብ ሌሊት ድረስ ምንም የወጣ መረጃ አልነበረም፡፡ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ የመንግሥት ተቋማትም መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሌሎች የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ጋር በአሸባሪነት መሰየሙ አይዘነጋም፡፡
 

Friday, March 6, 2015

ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ትግሉን ተቀላቀለ







ጋዜጠኛው በኢትዮጵያዊነቱ አያሌ በደሎች እንደ ተፈጸሙበት ያወጋል ! በተለይ ይላል ጋዚጠኛ አለምነህ ዋሴ ፍትህ እኩልነት በሌለባት ሃገሬ ጋዜጠኛ ርዩት ዓለሙ ላይ የተፈፀመው ኢሰባዊ ድርጊት ከሁሉም በላይ ከህሊናው ሊጠፋ የማይችል ዘግናኝና አረምኔያዊ ድርጊት መሆኑን ይገልጻል ። ጋዜጠኛው ልጆቹን ከማሳደግ ባሻገር ሃገሩ ላይ ሲኖር ደስተኛ እንዳ ልነበረ በመጥቀስ ክእንግዲ አለ ጋዜጠኛ አለምንህ ዋሴ « ፍትህ እኩልነትና ነጻነት እስኪሰፍን » ሃገር አለኝ ብዬ ፊቴን ወደ ኢትዮጵያ አልዞርም ብሏል ። ጋዜጠኛው ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጀት ገለልተኛ ሆኖ ወገኑን ማገልገል እንዳልቻለና የገዢው ስረአት ወሬ አቀባይ ሳይሆኑ ገለልተኛ ሆኖ በነጻነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰርቶ መኖር ለህልውና አደገኛ መሆኑን የራሱን ተሞክሮ በመጥቀስ ያብራራል። በስራው ላይ ይደረግበት በነበረ ጫና የማስታወቂያ ስራዎቹ ለአየር እንዳይበቁ በደል እስከመፈጸምና በሙያው በቀን 10 በር ብቻ ተከፍሎት እንዲሰራ የተገደደበት አጋጣሚ እንደነበረ ለኢሳት በሰጠው መረጃ አጋልጦል። ጋዜጠኛው በአሁኑ ሰዓት አስራኤል ውስጥ ስደት ቤቴ ብሎ መኖር የጀመረ ሲሆን ለኢሳት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዙሪያ ከኢህአ ዴግ መንግስት ባለስልጣናት በኩል ምንም የተባለ ነገር ባይኖረም ጋዜጠኛው ወደ ሶስተኛ ሃገር ካልተሸጋገረ የደህነት ሁኔታው እንደ ሚያሰጋቸው አይሌ ኢትዮጵያውያን ይገልጻሉ። መንግስት ጋዜጠኞች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ተስፋ መቁረጥ የሚሉ እንዚህ ታዛቢዎች ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ከተዋቂው ጋዜጠና ዳሪዎስ ሞዴና ነጋሽ፡መሃመድ ቀጥሎ የጋዜጠኛ አለምንህ ድምጹ በተፈጥሮ የህዝብን ልብ ሰብሮ የመግባት ሃይል ስላለው ምናልባት መንግስት ደልሎ አሊያም በሃይል ወደ ሃገር ሊመልሰው እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ ። ኢትዮጵያን ሃግሬ ጅዳ በዋዲ

Tuesday, March 3, 2015

ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ

የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ

በአበበ ገላው                                                 [PDF]
(አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን  ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።
የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።
በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ
Bruce Allen.jpg
ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።
ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።
—-